ክብርት ሔራን ገርባ የኢትዮጵያ ምግብ መድሃኒት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር

“በግልም ሆነ እንደተቋም የአቶ ወንዱ ሲደክሙለት የነበረውን  ዓላማ ለማሳካት ዝግጁ ነን”

በውጭም ሆነ በሀገር ውስጥ የሚኖሩ አቶ ወንዱን በሥራዎቻቸው የሚያውቋቸው ሁሉ  ሀዘናቸውን በተለያየ መንገድ መግለፃቸውን ቀጥለዋል፡፡ ባለፉት ዓመታት ከአቶ ወንዱ ጋር  በቅርበት አብረው ሲሰሩ የቆዩት  የኢትዮጵያ ምግብ መድሃኒት ባለስልጣን አመራርና ሰራተኞች በአቶ ወንዱ ቤት በመገኘት ቤተሰቦቻቸውን አፅናንተዋል፡፡  የኢትዮጵያ ምግብ መድሃኒት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ክብርት ሔራን ገርባ በግላቸውና ተቋሙን ወክለው ባስተላለፉት መልዕክት አቶ ወንዱ በልጃቸው ሞት ምክንያት የደረሰባቸውን ሐዘን ወደ መልካም አጋጣሚ በመለወጥ ማቲዎስ ወንዱ ፋውንዴሽንን አቋቁመው ብዙ ልጆችንና ቤተሰቦቻቸውን ህይወት ከመታደጋቸውም በላይ በአገራችን የፖሊሲ ለውጥ የሚያስፈልጋቸው ሥራዎች ላይ ብዙ ለውጥ ያመጡና እኛም ትልልቅ ሥራዎችን እንድንሰራ ያበረቱን ታላቅ ሰው ናቸው ሲሉ መስክረዋል፡፡

በውጭም ሆነ በሀገር ውስጥ የሚኖሩ አቶ ወንዱን በሥራዎቻቸው የሚያውቋቸው ሁሉ  ሀዘናቸውን በተለያየ መንገድ መግለፃቸውን ቀጥለዋል፡፡ ባለፉት ዓመታት ከአቶ ወንዱ ጋር  በቅርበት አብረው ሲሰሩ የቆዩት  የኢትዮጵያ ምግብ መድሃኒት ባለስልጣን አመራርና ሰራተኞች በአቶ ወንዱ ቤት በመገኘት ቤተሰቦቻቸውን አፅናንተዋል፡፡ 

የኢትዮጵያ ምግብ መድሃኒት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ክብርት ሔራን ገርባ በግላቸውና ተቋሙን ወክለው ባስተላለፉት መልዕክት አቶ ወንዱ በልጃቸው ሞት ምክንያት የደረሰባቸውን ሐዘን ወደ መልካም አጋጣሚ በመለወጥ ማቲዎስ ወንዱ ፋውንዴሽንን አቋቁመው ብዙ ልጆችንና ቤተሰቦቻቸውን ህይወት ከመታደጋቸውም በላይ በአገራችን የፖሊሲ ለውጥ የሚያስፈልጋቸው ሥራዎች ላይ ብዙ ለውጥ ያመጡና እኛም ትልልቅ ሥራዎችን እንድንሰራ ያበረቱን ታላቅ ሰው ናቸው ሲሉ መስክረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ምግብ መድሃኒት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ክብርት ሔራን ፣ አመራሮችና  ሰራተኞቻቸው በቤታቸው ተገኝተው ስላፅናኑዋቸው ምስጋና ያቀረቡት የአቶ ወንዱ ባለቤት ወ/ሮ አምሳለ በየነ አቶ ወንዱ በህይወት እያሉ ለህዝባቸው የሚቆረቆሩ ቤተክርስቲያንም መስጊድም የሚያሰሩ እንደነበሩ በማስታወስ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ የጀመሯቸው ስራዎች ፍሬ እንዲያፈሩ እገዛ እንዲያደርግ ጠይቀዋል፡፡