ማቲዎስ ወንዱ-የኢትዮጵያ ካንሰር ሶሳይቲ ከበጎ ፍቃደኞች ጋር በመተባበር የቡሄ በአልን በሶሳይቲው የማህበራዊና ስነ-ልቦና ማዕከል  ውስጥ ከህሙማንና  አስታማሚዎች ጋር በመሆን በደመቀ ሁኔታ ነሀሴ 13 አክብሯል፡፡ በዕለቱ በጎ ፈቃደኞች ሙልሙል ዳቦ፣ ድፎ ዳቦ፣ ችቦ እንዲሁም ቆሎ በማምጣት በዓሉን አክብረዋል፡፡ የበዓሉን ሃይማኖታዊ እንዲሁም ባህላዊ ስነ-ስርአትና ትውፊት በጠበቀ መልኩ የቡሄ ጭፈራዎችና ዝማሬዎችን በማቅረብ፣ የችቦ ስነ-ስርአት በማካሄድና ጅራፍ በማጮህ  ለበዓሉ ከፍተኛ ድምቀት ሰጥተውታል፡፡  በዕለቱ የሃይማኖት ልዩነት ሳይኖር  ከምንም በላይ አብሮነትና መተሳስብ ልቆ የታየበት ሆኖ አልፏል፡፡

ማቲዎስ ወንዱ-የኢትዮጵያ ካንሰር ሶሳይቲ ጊዜያቸውን፣ ገንዘባቸውን እንዲሁም ጉልበታቸውን ሰውተው በዓሉን በደመቀ ሁኔታ እንዲያከብር ለረዱት በጎ ፈቃደኞችና ለቦሌ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ሰንበት ተማሪዎችና አገልጋዮች ከፍተኛ ምስጋናውን ያቀርባል፡፡