ማቲዎስ ወንዱ- የኢትዮጵያ ካንሰር ሶሳይቲ ከኢትዮጵያ ተላላፊ ያልሆኑ ህመሞች ማህበራት ህብረት (ኢተያህማህ) እንዲሁም ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በኢትዮጵያ ተላላፊ ያልሆኑ ህመሞችን ሁኔታ ከሁሉን-አቀፍ የጤና ሽፋን (Universal Health Coverage) አንፃር የሚገኙበትን ሁኔታ የሚያሳይ ሪፖርት በጥር 16 ቀን 2015 ዓ.ም በኢንተር ለግዠሪ ሆቴል አቅርቧል።

በኢትዮጵያ ከጊዜ ወደ ጊዜ በመጨመር ላይ ከሚገኙት የተላላፊ ያልሆኑ ህመሞች ስርጭትና ተፅዕኖ በመነሳት ሪፖርቱ ተላላፊ ባልሆኑ ህመሞች ዙሪያ  የሚሰጡ የጤና አገልግሎቶች የፋይናንስ ሁኔታ፣ ተደራሽነትና ጥራት ከሁሉን-አቀፍ የጤና ሽፋን አንፃር ከማሳየቱም በተጨማሪ ሀገራችን ተላላፊ ያልሆኑ ህመሞችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር እንዲሁም ሁሉን አቀፍ የጤና ሽፋን ለመተግበር የምታደርገው እንቅስቃሴ ላይ የበኩሉን እገዛ ያደርጋል ተብሎ ይታመናል፡፡

                    

Mathiwos Wondu-YeEthiopia Cancer Society, in cooperation with Consortium of Ethiopian Non-Communicable Diseases Association (CENCDA) and Ministry of Health, held a report briefing on the status of non-communicable diseases in Ethiopia in terms of Universal Health Coverage, on January 24, 2023 at Inter Luxury Hotel.

 

 

 

 

 

Based on the increasing prevalence and impact of non-communicable diseases in Ethiopia, the report In addition to showing the financial status, accessibility and quality of health services provided around non-communicable diseases in terms of universal health coverage, it is believed to contribute a great deal to our country’s efforts to prevent and control non-communicable diseases and implement universal health coverage.