ወርቃማው መስከረም በየዓመቱ የሚከበር የህፃናት ካንሰር የግንዛቤ ማስጨበጫ ወር ነው።
የህጻናት ካንሰር ዋና ዋና ምልክቶችን ያውቋቸዋል?
- ራስ ምታትና በተደጋጋሚ ጠዋት ጠዋት ማስመለስ፣
- በተከታታይ ክብደት መቀነስ፣
- በየጊዜው በኢንፌክሽን መጠቃት እና አቅም ማጣት፣
- የማየት አቅም በድንገት መዳከም እና የታችኛው የዓይን ክፍል ነጭ መሆን
እነዚህን እና ሌሎች ምልክቶችን ሲያስተውሉ፣ እባክዎን አቅራቢያዎ ወደሚገኝ የጤና ተቋም በመሄድ ምርመራ ያድርጉ።
እናቴ፣ አባቴ፣ ወንድሜና እህቴ፤ ይህንን ታውቃላችሁ?
- በአሁኑ ሰዓት የህፃናት ካንሰር በፍጥነት እየጨመረና ህልማችንን እየቀጠፈ ይገኛል።
- እኛ የነገ ተስፋዎች፣ በካንሰር እንዳንሞትና ነገን በተስፋ እንድንኖር የእናንተ የጋራ ርብርብ ያስፈልገናል።
- እናንተ ስታበረቱን፣ እኛም እንጠነክራለን፤ ተስፋችን ይለመልማል፤ እንድናለንም!
ሁሌም ተስፋዎቻችን እናንተ ናችሁ።
Recent Comments