የጡት ካንሰር በሁሉም የአለማችን ክፍል በከፍተኛ ሁኔታ እያደገ የመጣና የሴቶችን ሕይወት እየቀጠፈ የሚገኝ ቁጥር አንድ በሽታ ነው
ለመሆኑ የጡት ካንሰር እንዴት ይከሰታል?
በርካታ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ለጡት ካንሰር የመጋለጥ ዕድልን የሚጨምሩ በርካታ ምክንያቶች ቢኖሩም የሚከተሉት ዋነኞቹ ናቸው
-
ዕድሜ- የሴቶች ዕድሜ እየጨመረ በመጣ ቁጥር በጡት ካንሰር የመጠቃት ዕድልም በዛው መጠን ይጨምራል
-
የዘረ-መል ለውጥ ሒደት – በሴቶች ጡት ውስጥ የሚከሰቱ የዘረ – መል ለውጥ ሂደቶች (BRCA 1እና 2) ለጡት እና ለእንቁላል ማምረቻ ክፍል በጡት ካንሰር የመያዝ እድልን ከፍ ያደረጋሉ
-
ዕድሜና እርግዝና- የመጀመሪያ እርግዝና ከ30 ዓመት በላይ ሲሆን ወይም ሴቶች ሳያረግዙ ከቆዩ ለጡት ካንሰር የመጋለጥ ዕድላቸው ይጨምራል
-
ከመጠን ያለፈ ክብደት
-
የጡት መጠን ከፍ ማለት
-
ሲጋራ ማጨስ
-
አልኮል አብዝቶ መጠጣት
በጡት ካንሰር የመያዝ ዕድልን እንዴት መቀነስ ይቻላል?
-
ጤናማ የአመጋጋብ ልምድ በማዳበር
-
አዘውትሮ የሰውነት እንቅስቃሴ በማድረግ
-
የአልኮል መጠጦችን መጥኖ በመውሰድ
-
ከመጠን ያለፈ ክብደትን በመቆጣጠር
-
የራስን ጡት በራስ የመመርመር ዘዴን በማዳበር
-
ቅድመ ምርመራ በማድረግ
ጡትን በራስ እጅ በመዳሰስ እንዴት ምርመራ ማድረግ ይቻላል?
ጡትን በራስ እጅ በመዳሰስ የሚደረግ ምርመራ ዘዴ የጡታችንን የጤንነት ሁኔታ ለመረዳት ያግዘናል፡፡
በዚህም በጡታችን ላይ የሚከሰት ለውጥን ማስተዋልና የሚሰማንን ስሜት መከታታል ያስችለናል፡፡ በዚህ ጊዜ የተለየ ለውጥ ከተሰማን ወዲያውኑ በቀጥታ ወደ ጤና ባለሙያ መሄድ ያስፈልጋል፡፡
Recent Comments