“ማቲዎስ ወንዱን እናመሰግናለን፤ አሁን የጡት ካንሰርን ከመፍራት ይልቅ መመርመር የተሻለ መሆኑን ተረድተናል”
ማቲዎስ ወንዱ_ የኢትዮጵያ ካንሰር ሶሳይቲ ለሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ላሜ ዴይሪ ሠራተኞች የጡት ካንሰር ግንዛቤ ማስጨበጫ እና ምርመራ አካሂዷል።
የማቲዎስ ወንዱ_ የኢትዮጵያ ካንሰር ሶሳይቲ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ወንዱ በቀለ ጤናማና ደስተኛ ህይወትን ስለመምራትና ተላላፊ ያልሆኑ ህመሞችን ስለመከላከል የህይወት ልምዳቸውን አካፍለዋል።
ስለካንሰር ምንነት ፣ መንስኤ፣ ህክምናና በተለይ የጡት ካንሰር በሀገራችን በከፍተኛ ሁኔታ እየተስፋፋ በመሆኑ አስቀድሞ መመርመርና ህክምናን መከታተል ተገቢ መሆኑን በማቲዎስ ወንዱ_ የኢትዮጵያ ካንሰር ሶሳይቲ ሜዲካል አስተባባሪ እና የካንሰር ሀኪም የሆኑት ዶ/ር ናትናኤል አለማየሁ አብራርተዋል።
በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የላሜ ዴይሪ ሠራተኞች ማቲዎስ ወንዱን እናመሰግናለን፤ አሁን የጡት ካንሰርን ከመፍራት ይልቅ መመርመር የተሻለ መሆኑን ተረድተናል ሲሉ ለተሰጣቸው የመማማርና የምርመራ ዕድል አመስግነዋል።
የላሜ ዴይሪ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ጋሻው ይመር ለፋብሪካ ዋናው ሀብቱ ጤናማ ሠራተኛ ነው ፤ ሶሳይቲው ለሠራተኞቻችን ጤና እንዳሰበው ሁሉ ድርጅቱም በቻለው ሁሉ ከሶሳይቲው ጎን ይቆማል ብለዋል።
Recent Comments