ማቲዎስ ወንዱ_ የኢትዮጵያ ካንሰር ሶሳይቲ ለሚድሮክ ኢትዮጵያ ሆራይዘን አዲስ ጎማ ሰራተኞች የጡት ካንሰር ግንዛቤ ማስጨበጫ እና ምርመራ ፕሮግራም አካሄደ።
የጥቅምት ወር የጡት ካንሰር ግንዛቤ ማስጨበጫ ወቅትን ምክንያት በማድረግ ማቲዎስ ወንዱ_ የኢትዮጵያ ካንሰር ሶሳይቲ ከቸርችል ጤና ጣቢያ ጋር በመተባበር ተላላፊ ያልሆኑ ህመሞች ግንዛቤ ማስጨበጫ እና ምርመራ አካሂዷል።
የማቲዎስ ወንዱ-የኢትዮጵያ ካንሰር ሶሳይቲ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ወንዱ በቀለ ተላላፊ ያልሆኑ ህመሞች በከፍተኛ ሁኔታ እየተስፋፉ በመሆኑ ህብረተሰቡ መጠንቀቅና ተመርመሮ ህክምናውን መከታተል ይገባዋል ብለዋል።
የማቲዎስ ወንዱ_ የኢትዮጵያ ካንሰር ሶሳይቲ ሜዲካል አስተባባሪና የካንሰር ሀኪም የሆኑት ዶ/ር ናትናኤል አለማየሁ ስለ ጡት ካንሰር ምንነት፣ መንስኤ፣ መከላከያ ዘዴ እንዲሁም ህክምናውን በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በሚድሮክ ኢትዮጵያ የሆራይዘን አዲስ ጎማ ሠራተኞች ተላላፊ ያልሆኑ ህመሞችን በተመለከተ እንዲሁም ስለ ጡት ካንሰር በተደረገላቸው ገለፃና በጥያቄና መልስ ባገኙት ዕውቀት የተሻለ ኝዛቤ እንዳገኙ ተናግረው ለተደረገላቸው የደም ግፊትና የስኳር እንዲሁም የጡት ካንሰር ምርመራ ሶሳይቲውን አመስግነዋል።
Recent Comments