በዚህ ዓመት መሪ ቃሉ “የስኳር ህመምና ደህንነት፤ በስራ ቦታ ስለ ስኳር ህመም ይበልጥ ይገንዘቡ ተጨማሪ ድጋፍ ያድርጉ ” የሚል ነው፡፡
የዓለም የስኳር ህመም ቀን በየአመቱ ህዳር 5 በዓለማቀፍና በሀገርአቀፍ ደረጃ ሲከበር ስለ ስኳር በሽታ፣ ስለበሽታው መከላከል እና የተሻሻለ የስኳር ህክምና አገልግሎትን አስፈላጊነት ግንዛቤ ለማስጨበጥ ነው። የስኳር ህመም በአለም ዙሪያ ባሉ ግለሰቦች፣ ቤተሰቦች እና ማህበረሰቦች ላይ የሚኖረውን ከፍተኛ ተጽእኖ ለማስታወስም ያገለግላል።
የኢትዮጵያ ስኳር ማህበር ባዘጋጀው ዓመታዊ የስኳር ህመም መታሰቢያ መርሐግብር ላይ የማቲዎስ ወንዱ ፋውንዴሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ ተገኝተዋል።
የስኳር ህመም በሁሉም ዕድሜ ሊያጋጥም የሚችል የጤና ችግር ሲሆን ያልተቆጣጠሩት የስኳር ህመም ለአይነስውርነት ፣ ለኩላሊት ስራ ማቆም፣ ለልብ ህመም ፣ ለደምግፊትና ለሌሎችም የተወሳሰበ የጤና ችግር ይዳርጋል።
በዓለማችን ግማሽ ያህሉ ታማሚዎች የስኳር ህመም እንዳለባቸው ባለማወቃቸው መድሀኒት እንደማይወስዱ የዓለም ጤና ድርጅት መረጃ ይጠቁማል።
በ1990 የስኳር ህመም ያለባቸው ሰዎች ቁጥር 200 ሚሊየን የነበረ ሲሆን በ2022ደግሞ 830 ሚሊየን ሰዎች ከስኳር ህመም ጋር ይኖራሉ።
Recent Comments