ወርቃማው መስከረም በየዓመቱ የሚከበር የህፃናት ካንሰር የግንዛቤ ማስጨበጫ ወር ነው። 

የህጻናት ካንሰር ዋና ዋና ምልክቶችን ያውቋቸዋል?

  • ራስ ምታትና በተደጋጋሚ ጠዋት ጠዋት ማስመለስ፣
  • በተከታታይ ክብደት መቀነስ፣
  • በየጊዜው በኢንፌክሽን መጠቃት እና አቅም ማጣት፣
  • የማየት አቅም በድንገት መዳከም እና የታችኛው የዓይን ክፍል ነጭ መሆን

እነዚህን እና ሌሎች ምልክቶችን ሲያስተውሉ፣ እባክዎን አቅራቢያዎ ወደሚገኝ የጤና ተቋም በመሄድ ምርመራ ያድርጉ።

እናቴ፣ አባቴ፣ ወንድሜና እህቴ፤ ይህንን ታውቃላችሁ?

  • በአሁኑ ሰዓት የህፃናት ካንሰር በፍጥነት እየጨመረና ህልማችንን እየቀጠፈ ይገኛል።
  • እኛ የነገ ተስፋዎች፣ በካንሰር እንዳንሞትና ነገን በተስፋ እንድንኖር የእናንተ የጋራ ርብርብ ያስፈልገናል።
  • እናንተ ስታበረቱን፣ እኛም እንጠነክራለን፤ ተስፋችን ይለመልማል፤ እንድናለንም!

ሁሌም ተስፋዎቻችን እናንተ ናችሁ።