ማቲዎስ ወንዱ-የኢትዮጵያ ካንሰር ሶሳይቲ ከዓለም ጤና ድርጅት፣ መቋሚያ፣ ከጤና ልማትና ፀረ-ወባ ማህበር እንዲሁም የምግብና መድሃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ጋር በመሆን  የዓለም ከትምባሆ ነፃ ቀንን በማስመልከት የፓናል ውይይት ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው የመንግስት መስሪያ ቤቶችና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በተገኙበት በግንቦት 23 ቀን 2014 ዓ.ም በአዲስ አበባ ኢንተርለግዠሪ ሆቴል አካሂዷል፡፡

የዓለም ከትምባሆ ነፃ ቀን በየአመቱ የትምባሆ አጠቃቀም ላይ ግንዛቤን ለማሳደግና ማቆምን ለማበረታታት የሚከበር አመታዊ ቀን ነው። ቀኑ በዓለም ለ35ተኛ ጊዜ በአገራችን ደግሞ ለ30ኛ ጊዜ የሚከበር ሲሆን በዚህ አመትም “ከትምባሆ ጭስ በፀዳ አካባቢ መኖር ተፈጥሯዊ መብቴ ነው” በሚል መርህ ተከብሯል፡፡

በውይይቱ ወቅት በኢትዮጵያ ከትምባሆ አጠቃቀምና ቁጥጥር ጋር የተያያዙ ተግዳሮቶች  እንዲሁም በሀገራችን የትምባሆ አጠቃቀምና ቁጥጥር ያለበት ደረጃ ተዳሰዋል።

A panel discussion on World No Tobacco Day with the theme of “Living in a non-smoking environment is my birth right” was conducted. 

Mathiwos Wondu-YeEthiopia Cancer Society in collaboration with the World Health Organization, Health Development and Anti-Malaria Association, Mekuamiya, and Ethiopian Food and Drug Authority conducted a panel discussion with government bureaus and non-governmental organizations regarding World No Tobacco Day on May 31, 2022, at Inter Luxury Hotel, Addis Ababa.

World No Tobacco Day is an annual event to raise awareness of tobacco use and encourage quitting. World No Tobacco Day is celebrated for the 35th time in the world and for the 30th time in our country with the theme of “Living in a non-smoking environment is my birth right”. During the discussion, challenges related to tobacco use and control in Ethiopia, and the current status of tobacco use and control in the country were explored and discussed.